Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አስተባባሪነት “አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ “በሚል ከ35ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 16 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አስተባባሪነት “አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ “በሚል 35 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባንኮቹ የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባንኮች እና የመድህን ዋስትና (ኢንሹራንስ) ተቋማት የከተማውን ኢኮኖሚ በማንቀሳቀስ እና ልማቱ እንዲፋጠን ጉልህ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አስተባባሪነት “አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ “በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ ድጋፍ 18 ባንኮች፣ የአዋሽ ባንክ ሠራተኞች እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጠቅላላ 35 ሚሊየን 330 ሺህ711 ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.