Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ኒውክሌርን ለሰላማዊ ዓላማ ማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ኒውክሌርን ለሰላማዊ ዓላማ ማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ።
አዋጁ የጸደቀው ዛሬ በተካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ነው፡፡
ስምምነቱ የዕውቀት ሽግግርን ለመፍጠር የሚያግዝ፣ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚያደርግ እና ይህን የሚደግፉ አሰራሮች የማበጀት ግዴታ የሚጥል ነው
ሀገሪቱም የሀይል አማራጭ እንዲኖራት የባለሙያወችን አቅም ለመገንባት እና ልምድ ለመለዋወጥ ያግዛልም ነው የተባለው።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ከህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።
በአፈወርቅ አለሙ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.