Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለአንድ ወር የሚቆይ ልዩ የጸሎትና የንሰሃ መርሃ ግብር ታወጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በመላ የሃገራችን ክፍል ተግባራዊ የሚሆን ወቅታዊውን የኮሮና ወረርሽኝን በማስመልከት ለመላው ምዕመናን ሃገራዊ የጸሎት ጥሪ አስተላልፈዋል።
 
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች፥ ከመጋቢት 28፣ 2012 ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ በመላው የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በቤታቸው ሆነው በጸሎት የፈጣሪን ምህረት የሚለምኑበት ጊዜ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
 
በዚህም መሠረት በነገው ዕለት በሶስት የተመረጡ ቦታዎች የጸሎት መርሃ ግብሩ የማስጀመርያ ፕሮግራም ይከናወናል ተብሏል፡፡
 
በዚህ ፕሮግራም ላይ የኃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና ወጣቶች ተሳታፊ ይሆናሉም ነው የተባለው፡፡
 
ወሩን በሙሉ በተመረጡ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚወጣው መርሃ ግብር መሠረት÷ የሃይማኖት አባቶች የሚያደርጉት ልዩ የጸሎትና የትምህርት ፕሮግራም ለህዝቡ በቀጥታ የሚተላለፍ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.