Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሚፈጠሩ ግጭቶች ከህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ጋር የተገናኙ ናቸው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚፈጠሩ ግጭቶች ከህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ጋር እንደሚገናኙና ለዚህም ተገቢውን መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ምሁራን አመላከቱ፡፡
የህዳሴ ግድብ ሙሌት ወቅትን ጠብቀው የሚወረወሩት አጀንዳዎች ሕዝቡን ለማሸበር እና መንግስት እንዳይረጋጋ ለማድረግ እንደሆነ ምሁራኑ አብራርተዋል።
የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ደያሞ ዳሌ÷ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጠሩ ግጭቶች እና ሕዝብን በሕዝብ ላይ እንዲነሳ የሚጋብዙ የንፁሃን ግድያዎች ሕዝብና መንግስት እንዳይረጋጉ የሚያደርጉ ሴራዎች በመሆናቸው እንደዋዛ መታየት የለባቸውም ነው ያሉት፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አወል አሊ እንዲሁ ÷ በየጊዜው በሚጎነጎኑ የግጭት ሴራዎች ሕዝቡ ሰለባ እንዳይሆን መንግሥት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።
የግድቡን የውሃ ሙሌት የማሰናከል አጀንዳን መረዳት ችግሩን ለመቀነስ እንደሚረዳ አበክረው የሚናገሩት ምሁራኑ፣ ወደ ሁከት የሚወስዱ መንገዶችን ማጥናትና መፍትሄ መስጠት ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑንም ጠቁመዋል።
በሃይማኖት ወንድራድ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.