Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 766 ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 766 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ትናንት በ24 ሰአታት ውስጥ ለ3 ሺህ 922 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 206 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውም አስታውቋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 139ኙ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፤ 30 ከጋምቤላ ክልል እንዲሁም 10 ደግሞ ከድሬዳዋ በመሆን ከፍተኛ ቁጥር ማስመዝገባቸውን ገልጿል።

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 250 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 4 ሺህ 556 መድረሱንም ነው የጤና ሚኒስቴር የላከልን መረጃ የሚያሳየው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.