Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ20 ሺህ በላይ ሲሆን ህይወታቸው ያለፈ ደግሞ 356 ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 29 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ በተካሄደው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ 20 ሺህ 336 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።
 
ባለፉት 24 ሰዓታት ለ7 ሺህ 319 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎ 459 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
 
ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 336 ደርሷል።
 
ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎም በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 356 ሊደርስ ችሏል።
 
በአሁን ወቅት በፅኑ የታመሙ 185 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
 
ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳሰፈሩት ባለፉት 24 ሰዓታት 358 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።
 
ኢትዮጵያ እስከ አሁን ደረስ ለ459 ሺህ 746 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ ችላለች።
 
ከእነዚህም መካከል 8 ሺህ 598 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን 11 ሺህ 380 የሚሆኑት የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.