Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ70 ሺህ አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ70 ሺህ ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 813 የላብራቶሪ ምርመራ 713 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 70 ሺህ 422 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ባለፈ የ19 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 127 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 357 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ 991 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 217 ሺህ 746 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 70 ሺህ 422 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 40 ሺህ 302 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 251 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 28 ሺህ 991 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ1 ሺህ 127 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.