Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ዳስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተመራው ልዑክ በሪያድና አከባቢዋ ከሚኖሩ የዳየስፖራ ማህበረሰብ ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ዳስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተመራው የልዑካን ቡድን በሪያድና አከባቢዋ ከሚኖሩ የዳየስፖራ ማህበረሰብ ጋር ተወያየ።
የልዑካን ቡድኑ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች፣ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጂንሲ እየተከናወኑ ባሉ ዋና ዋና ስራዎችና በዜጎች ጉዳይ ላይ ውይይት ያካሄደው፡፡
በሪያድና አከባቢው ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ህግን ለማስካበር በግንባር ከፍተኛ ተጋድሎ እየፈጸመ ለሚገኘው ለሃገር መከላከያ ሠራዊት 72 ሺህ 500 ሪያል ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ 42 ሺህ 700 ሪያል ቃል ተገብቷል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በጀዳና አከባቢው የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላትም ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ አድርገዋል።
ቡድኑ በእስከ አሁኑ ቆይታው ከኢትዮጵያ የሪያድ ኤምባሲ እና ጀዳ ጀኔራል ቆንስላ ጽህፈቤት ኃላፊዎችና ዲፕሎማቶች፣ በጀዳና አከባቢው ከሚኖሩ የኮሙኒቲ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ በጀዳ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የኮሙኒቲ ትምህር ቤት ቦርድ አባላት፣ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በጀዳ የሽሜሲ ማቆያ ማዕካል ከፍተኛ ሃላፊዎችና በሪያድ የዋፊድንና ስጃን ማቆያ ማዕከላት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይቷል።
በቀጣይም ከጀዳ፣ ከጂዛን እና መካ የኮሙኒቲ ተወካዮች ጋር ይወያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከዲያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.