Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች የኮሮናቫይረስ ስትራቴጂ ቀርጾ ከመንግሥት ጋር እየሰራ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የድንበር ተሻጋሪና የአገር አቋራጭ አሽከርካሪዎች የኮሮና ቫይረስ ስትራቴጂ ቀርጾ ከመንግሥት ጋር እየሰራ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል።

ድንበር ተሻጋሪና የአገር አቋራጭ አሽከርካሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ከሚባሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ብሏል።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮ የድንገተኛ ሕክምና ኦፊሰር ዶክተር አማረ ወርቅዬ እንደገለጹት ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር በመቀናጀት አሽከርካሪዎቹ ለቫይረሱ ያላቸው ተጋላጭነትን የሚከላከሉበት ስትራቴጂ ቀርጿል።

የስትራቴጂው ዋነኛ ትኩረት አሽከርካሪዎቹ ራሳቸውን በቫይረሱ እንዳይያዙና ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ መከላከል መሆኑን አስረድተዋል።

አሽከርካሪዎቹ ያላቸውን እንቅስቃሴ መለየትና በሚያርፉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የጤና ተቋማት እየተለዩ መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.