Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ጨዋታ ሙጀብ ቃሲም የፋሲል ከነማን የአሸናፊነት ግብ ሲያስቆጠር÷የአሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ ቡድን በ 9 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞውን አስቀጥሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከነማ  ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ በመቀነስ የመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ይበልጥ ተጠባቂ ሆነዋል።

ለፋሲል ከነማ ወሳኝ ተጨዋች መሆኑን እያሳየ የሚገኘው ሙጅብ ቃሲም ÷ በተከታታይ ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች 3 ግብ በማስቆጠር የቡድኑ ባለውለታ መሆን ችሏል፡፡

በተመሳሳይ ረፋድ ላይ በተደረገ መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ በአህመድ ሁሴን ብቸኛ ጎል ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ከጨዋታው በኋላ የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ናስር በይፋ ከክለቡ ጋር የተለያየ ሲሆን÷ በቀጣይ የደቡብ አፍሪካውን ክለብ ማማሎዲ ሰንዳውንስን የሚቀላቀል ይሆናል፡፡

ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዳቸውን አረጋግጠዋል። ሶስተኛው ወራጅ ቡድን በቀሪ መርሐ ግብሮች የሚለይ ይሆናል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.