Fana: At a Speed of Life!

በኢኳቶሪያል ጊኒ በደረሰ ፍንዳታ 15 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢኳቶሪያል ጊኒ በተከሰተ ተከታታይ ፍንዳታ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡
ባታ በተባለው ከተማ በደረሰው ፍንዳታ ሕይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 500 ሰዎች ቆስለዋል ነው የተባለው፡፡
የሃገሪቱ መንግስት ፍንዳታው የተከሰተው በወታደራዊ የጦር ሰፈር ውስጥ በድማሚት ማስቀመጫ ስፍራ “በተፈጠረ ቸልተኝነት” ነው ብሏል ፡፡
ከዚህ ባለፈ ግን ምናልባትም አርሶ አደሮች በጦር ሰፈሩ አካባቢ ያለውን ሜዳማ ስፍራ ማቃጠላቸው ለፍንዳታው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል፡፡
በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎችን ህይወት የመታደግ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከፍንዳታ ጋር ተያይዞም መንግስት ዓለም አቀፍ እርዳታ ጠይቋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.