Fana: At a Speed of Life!

በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በቂ የተማረ የሰው ሃይል እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በቂ የተማረ የሰው ሃይል መኖሩ ለዘርፉ እድገት አብርክቶ እንደሚኖረው የኦሮሚያ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ኤጀንሲ ገለጸ፡፡
ኤጀንሲው ከግብርና ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልሉ የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት (LFSDP) አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር የመስክ ጉብኝት በጅማ ዞን አካሂዷል።
በጉብኝቱ የሊሙ ኮሳ እና የቀርሳ ወረዳዎች በመደበኛ እና በእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎች ተጎብኝተዋል፡፡
በወረዳዎቹ ከተጎበኙት ስራዎች መካከል በአርሶ አደሮች እና በተደራጁ ወጣቶች የተሰሩ የበጎች እና ፍየሎች ማደለብ ስራ፣ የዶሮ እርባታ፣ የመስኖ ልማት፣ የንብ ማነብ እና የዓሳ ማስገር ስራዎች ናቸው።
በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ (LFSDP) ብሄራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት እንደገለፁት በፕሮጀክቱ ድጋፍ የተደራጁ ወጣቶች በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በመስራት የድጋፍን ውጤታማነት በተጨባጭ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡
በዘርፉ የተሰማሩ አካላትም ወደ ተሻለ የኢንቬስትመንት ስራ እንዲገቡ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልሉ እንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ኤጀንሲ ምክትል ሃላፊ አቶ ታመነ ባልቻ በበኩላቸው የተማሩ ወጣቶች ተደራጅተው ከመንግስት ድጋፍ ሲያገኙ የራሳቸውን ስራ መፍጠር እንደሚችሉ ተናግረዋል።
በዘርፉ የተማረ ሃይል መኖሩ መንግስት ከተሰጠው ትኩረት ጋር ተዳምሮ ለዘርፍ ዕድግ የሚኖረው አብርክቶ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
በጉብኙቱ ላይ የተሳተፉት በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ሚንስቴር ዴኤታ ዶ/ር ፍቃዱ ረጋሳ በበኩላቸው በሁለቱም ወረዳዎችና በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እየጨመረ ያለውን የህዝብ ቁጥር እና የእንስሳት ምርት ፍላጎት ሊያሙሉ የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የመንግስት ትኩረት የእንስሳት ዘርፉን ምርታማነት ለመጨመር እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሚታን ለማሳደግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በአስር ዓመት መሪ እቅድ ውስጥ ዘርፍ ላይ መስረታዊ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት ለመስራት መታቀዱን አስረድተዋል፡፡
ጉብኝቱን ከተጠናቀቀ በኋላ በተደረገ ውይይት ላይ ለዘርፉ በቂ ትኩረት ያልተሰጠው መሆኑ ተነስቷል፡፡
በተለይም የሎጂስትክስና የግብዓት አቅርቦት እጥረት በተለይ የእንስሳት መኖ እና የሰው ሰራሽ የማዳቀል ስራ፥ የዶሮ እርባታ ሌሎች ግብዓቶች ላይ ያለውን እጥረት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ሊፈታው ይገባል ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.