Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት የኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ ጉዳት በመድረሱ ዜጎች ስራ የማጣት ስጋት እንደተደቀነባቸው ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የቻሉ ኢንቨስትመንቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የስራ እድሉ ተጠቃሚዎች በጥፋት ሀይሎች በተፈፀመው ድርጊት ስራ የማጣት ስጋት ወስጥ መውደቃቸውን ገልጸዋል።

በድርጅቶች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶቹ መንግስት ይህን ድርጊት የፈጸሙ አካላትን ለህግ የማቅረቡን ስራ እንዲቀጥል እና ህብረተሰቡም በጋራ የራሱን ሀብት የመጠበቅ ልምዱን ሊያጠናክር እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከሼር ኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ልማት ድርጅት እንዳገኘነው መረጃ ከውድመቱ በፊት 3 ሚሊየን አበባ በቀን ለአለም አቀፉ ገበያ የሚያቀርበው ስራው በግማሽ ቀንሷል።

የኦሮሚያ ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀይሉ ጀልዱ  ጉዳት የደረሰባቸው ኢንቨስትመንቶችን ዳግም ወደ ስራ ለማስገባት የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል፤ ከጎናቸውም ነው ብለዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የሆርቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ወንድአለ ሀብታሙ÷ ኢትዮጵያ ከአበባ ልማት ዘርፍ እስከ 420 ሚሊየን ዶላር ገቢን እያገኘች እንደመሆኑ ይህን መሰል ጉዳት እንዳይደርስ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል።

 

በሀይለየሱስ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.