Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ለተቸገሩ ወገኖች ከ27 ሺህ 900 ኩንታል በላይ እህል ተከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ለተቸገሩ ወገኖች ከ27 ሺህ 900 ኩንታል በላይ እህል ለተጎጂዎች መድረሱን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በአካባቢው ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ሳቢያ በተከሰተው ድርቅ ነዋሪዎች ለችግር ተዳርገዋል።
ይህንንም ተከትሎ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ችግረኞችን ለመርዳት በተለይም አስቸኳይ የምግብ እህል አቅርቦት እንዲያገኙ አድርጓል ብለዋል።
በአገሪቱ ቆላማና ድርቅ በተከታታይ ከሚያጠቃቸው አካባቢዎች መካከል የቦረና ዞን አንዱ መሆኑን ገልፀው ኮሚሽኑ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም በዞኑ በተከሰተው ድርቅ ለተቸገሩ ወገኖች ከ27 ሺህ 900 ኩንታል በላይ እህል ለተጎጂዎች መድረሱን ገልጸዋል።
ከዚህ ውስጥ 12 ሺህ 400 ኩንታል በላይ ስንዴ፣ ከ6 ሺህ ኩንታል በላይ ሩዝ፣ 6 ሺህ ኩንታል ዱቄት እና ከ3 ሺህ 500 ኩንታል በላይ አልሚ ምግብ መሆኑን አቶ ደበበ አብራርተዋል።
ድጋፉ የመጀመሪያ ዙር መሆኑን ገልጸው በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
የድርቅ አደጋው በዞኑ አሁን ያለበትን ሁኔታ፣ የተጎጂዎችን ቁጥርና ሌሎች ተዛማች ጉዳዮችን የሚያጠና ቡድን ወደ ስፍራው ተልኮ መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆኑንም የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ለተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋ ከተጋለጡ ዜጎቿ መካከል 70 በመቶ የሚሆኑትን በራሷ አቅም እየረዳች መሆኑ ይታወቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.