Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አዘጋጅነት ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
በኮንፈረንሱም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ቀንአ ያዴታ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ህግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ ጨምሮ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኮንፈረንስ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ኮምሽነር ጌታቸው ኢታና ናቸው።
በዚሁ ወቅት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በፖሊስ ሳይንስ ትምህርት በሰርተፊኬት፡ በዲፕሎማ፡ በዲግሪ እና በማስተርስ መርሃ ግብር እንዲሁም በተለያዩ ሙያዎች የክልሉን ፖሊስ ሀይል በማስተማርና በማሰልጠን ብቁና በስነ-ምግባር የታነጹ የፖሊስ አባላትን በማፍራት የክልሉንና የሀገራችንን ሰላምና ጸጥታ የተረጋጋ እንዲሆን እየሰራ እንደሆነ ረዳት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የፖሊስ ሳይንስና ሰላም፣ ደህንነት እና የሰላም ግንባታ ፣ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት፣ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ጉዳዮች እንዲሁም በዓለማችን ሰላም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ጥናታዊ ፅሁፍ በምሁራን ቀርቦ ውይይት እንደተካሄደበት ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.