Fana: At a Speed of Life!

በከተሞች የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራምን ወደ 117 ከተሞች ማሳደግ ተችሏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በ44 ከተሞች ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ከ44ቱ ከተሞች በተጨማሪ የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አዳዲስ 73 ከተሞችን ጨምሮ መዳረሻውን በ117 ከተሞች ማስፋቱን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በ859 ሚሊዮን ዶላር በጀት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

የከተሞችን ተቋማዊና የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራምን ውጤታማ ለማድረግ አመራሩ በፕሮግራሙ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል ተብሏል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ዙሪያ ከሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች በቢሾፍቱ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መደረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በፕሮግራሙ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ማሻሻያ፣ ፈንድ ሞቭላይዜሽንና ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አምላኩ አዳሙ እንደተናገሩት በክልሉ በፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑ ሶስት ከተሞች መኖራቸውን ጠቁመው ፕሮግራሙን በዕውቀት ለመምራት ክልሉ እንደ አዲስ የተዋቀረ በመሆኑ ወደ ክልሉ የመጡ አዳዲስ አመራሮች በፕሮግራሙ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዘርፉ የቢሮ ሃላፊዎች፤ የዞን አመራሮች፤ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ከተሞች እንዲሁም ከንቲባዎችና ስራ አስኪያጆች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ፕሮግራሙ ከታህሳስ 03 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በመድረኩ የከተማ ልማት ፖሊሲን ጨምሮ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይት የሚደረግ ይሆናል፡፡

የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ULGDP I and II ) በ44 ከተሞች ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በተጨማሪ የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አዳዲስ 73 ከተሞችን ጨምሮ መዳረሻውን በ117 ከተሞች በማስፋት በ859 ሚሊዮን ዶላር በጀት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.