Fana: At a Speed of Life!

በከፍተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ብቻ አሸባሪው ህወሓት ባደረገው ወረራ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማውደሙ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (2014) በከፍተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ብቻ አሸባሪው ህወሓት ባደረገው ወረራ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማውደሙን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በምስራቅ አማራ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት በደሴ ከተማ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከወረራው በኋላ የደረሰውን ጉዳት አጥንቷል።

በጥናቱ መነሻነትም በቀጣይ ከመንግስት በኩል ምን አይነት ድጋፍ ይጠበቃል የሚለው በየዘርፉ ተለይቶ በፌደራል ደረጃ ለተቋቋመ ኮሚቴ ቀርቧል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለው በበኩላቸው፥ የክልሉ መንግስት በጦርነት ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የክልሉን ፀጥታና ሰላም ማረጋገጥ እንዲሁም የልማትና የኢንቨስትመንት ተግባራትን ማጠናከር ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውንም አክለው ገልፀዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት እና ባለሀብቶች ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.