Fana: At a Speed of Life!

በካሜሩን በተፈጸመ ጥቃት 22 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን ምዕራብ ካሜሩን በአንድ መንደር ላይ በተፈጸመ ጥቃት 22 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

ከተገደሉት መካከል ግማሸ የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩም ነው የተገለጸው።

አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ለጥቃቱ የሃገሪቱን ጦር ተጠያቂ ቢያደርጉም፥ የጦር ሰራዊቱ አባል የሆኑ የጦር መኮንን ደግሞ ውንጀላውን ውድቅ አድርገዋል።

ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በመንግስት ወታደሮችና በተገንጣይ ቡድኖች መካከል ግጭት ተቀስቅሷል።

ተገንጣይ ቡድኖች አካባቢውን አምባዞኒያ የሚል ስያሜ በመስጠት ለነጻነት መንቀሳቀስ መጀመራቸው ለግጭቱ መንስኤ መሆኑ ይነገራል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከ3 ሺህ በላይ ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ ከ70 ሺህ የሚልቁት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

የካሜሩን መንግስት በግጭቱ ወቅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል በሚል ክስ ቢቀርብበትም፥ መንግስት ግን ተገንጣይ ቡድኖች በርካታ ንጹሃን እና የፀጥታ ሃይሎችን ገድለዋል በሚል ውንጀላውን ያስተባብላል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም አሜሪካ ከካሜሩን ጋር ያላትን ልዩ የንግድ መርሃ ግብር አቋርጠዋል።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.