Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
 
በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በካቱንዱ፣ ኪያምቡ፣ ቲካ፣ ጊጊሪ፣ጁጃ እና ሩይሩ ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 117 ዜጎቻችንን ከኬንያ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመተባበር ወደ ሀገራቸው እየመለሰ ይገኛል፡፡
 
በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 60 ወጣቶች በሞያሌ በኩል ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን÷ ቀሪዎቹ በቀጣዮቹ ቀናት በሁለተኛ ዙር እንደሚመለሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኤምባሲው ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ተገኝቶ የቆንስላ ጉብኝት በማድረግ ከሚመለከታቸው የኬንያ ባለስልጣናት ጋር ዜጎቹን በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጉ ይታወሳል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.