Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ አገልግሎት ለማግኘት የኮቪድ 19 ክትባት መውሰድ ግዴታ ሊሆን ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ በማንኛውም የመንግስት ተቋም አገልግሎት ማግኘት የሚፈልግ ሰው የኮቪድ 19 ክትባት መውሰድ አለበት ተብሏል፡፡

የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ በናይሮቢ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት እርምጃው በሀገሪቱ ያለውን የኮቪድ 19 ሁኔታ በመገምገም ቫይረሱን ለመቆጣጠር በማሰብ የተወሰደ ነው፡፡

ለ50 ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም የንግድ ተቋማት የክትባት ማረጋገጫ እንዲያቀርቡም ይጠየቃሉ፡፡

አዲሱ መመሪያ ከፈረንጆቹ ታህሳስ 21 ጀምሮ የሚተገበር ሲሆን፥ ማንኛውም ሰው የኮቪድ ክትባት መከተቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል ተብሏል፡፡

የአሁኑ እርምጃ በተለይም ከፈረንጆቹ የዘመን መለወጫ አከባበር ጋር በተያያዘ ሊኖር የሚችልን የቫይረሱን መዛመት ለመቀነስ እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

ከአዲሱ መመሪያ ጋር በተያያዘ ወደ ፓርኮች፣ ሆቴሎችና መሰል ሰው ወደሚበዛባቸው ቦታዎች መግባት የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ የኮቪድ ክትባት መውሰዱን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማሳየት ይኖርበታል፡፡

በኬንያ 254 ሺህ 710 ሰዎች ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን፥ 5 ሺህ 328 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን ሺንዋን ዋቢ አድርጎ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.