Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 48 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 29 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኬንያ 48 የአንድ ቤተሰብ አባላት የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር የቤተሰቡ አንድ አባል የውጭ ሀገር ጉዞ አድርጎ እንደነበረ ነው ያስታወቀው።

የዚህ ቤተሰብ አባል የሆኑ የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ እስከ ቤት ሰራተኛ ድረስ ያሉ የቤተሰቡ አባላት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሯል።

ጎርዶን ኦጎላ የተባለ የቤተሰቡ አባል የ61 ዓመቱ ታላቅ ወንድሜ በሽታውን መቋቋም ባለመቻሉ በ24 ሰዓታት ውስጥ ህይወቱ አልፏል ብሏል።

ኬንያዊያን የኮሮና ቫይስን ለመከላከል መንግስት ያስቀመታቸውን ተግባራት በተገቢው መንገድ ተግባራዊ እያደረጉ አለመሆኑ ይነገራል።

በዚህ ቤተሰብ ላይ የተከሰተው አጋጣሚም ኬንያዊያን ሊያስተምር ይገባል መባሉን ዴይሊ ኔሽን እና ዘ ስታር በዘገባቸው አስፍረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.