Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ዘንድሮ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በዘንድሮ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ።
 
የደቡብ ክልል የአካባቢ ጥበቃ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ባለስልጣን እንደገለፀው፥ የዚህ ዓመት አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን በቀጣዩ ሳምንት ግንቦት 28 ደቡብ ክልል ሀዋሳ ይጀመራል።
 
የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ግዛቴ ግጄ እንዳሉት የተፈጥሮ አካባቢ ብክለትና ጉዳት ጉዳይ የማይመለከተው ስለሌለ እና የችግሩ ባለቤትም ማህበረሰቡ በመሆኑ መፍትሄውን ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል።
 
እንደ ክልልም 1 ነጥብ 5 ቢሊየን የሚሆኑ ችግኞችን የመትከያ ቦታዎች የተዘጋጁ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ እስከ አሁን ባለው ሂደትም በክልሉ 50 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል።
 
በባለፈው አመት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥም 84 በመቶ ያህሉ መጽደቃቸው ነው የተነገረው ።
 
በሌላ በኩል የአለም አካባቢ ቀን ሀገር አቀፍ ፕሮግራም በዚህ አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ በሀገራችን ደግሞ “አካባቢን መጠበቅ የብዝሃ ህይወት ሀብትን መጠበቅ ነው” በሚል መሪ ቃል ለ27ኛ ጊዜ በደቡብ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ እንደሚውልም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.