Fana: At a Speed of Life!

በክምችት ያሉ የግብርና ምርቶችን ለአለም ገበያ በማቅረብ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በክምችት ያሉ የግብርና ምርቶችን ለአለም ገበያ በማቅረብ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባ ተገለጸ።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውን እና የበርካታ ዓለም ክፍልን እየተፈታተነ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአገራችን የወጪ ንግድ ላይ የሚያሳርፈውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመቋቋም በመንግስት በኩል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉም ነው የተባለው ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ዘርፉን ሊያጋጥመው ከሚችለው ጉዳት ለመታደግ  በርካታ የክትትልና የድጋፍ ስራ በመስራትላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በዚህም ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በዘርፉ እየተመዘገበ ያለው አፈጻጸም ከመቸውም ጊዜ በላይ የተሻለ መሆኑንና ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልም በግሉ ዘርፍ መጋዘኖች ውስጥ ባለው የምርት ክምችት ላይ ምልከታ አድርጓል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክፍተኛ አመራሮች የተደረገው የመስክ ጉብኝት የበሽታውን ስርጭት ተከትሎ ያለው የአለም ገበያ ሁኔታ ለሀገሪቱ የግብርና ምርቶች መልካም አጋጣሚ የፈጠረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በግሉ ዘርፍ መጋዘኖች ውስጥ ያሉ ክምችቶች የምርት ዘመናቸውን ጠብቀው በቀሪ ጊዜ ለገበያ በማቅረብ የገበያ እድሉን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ከዚያም ባለፈ  በዘርፉእያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፈተሽ ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት መሆኑንም በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጠቁመዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ የበሽታው ስርጭት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ በግብና ምርቶች ለማካካስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው  ብለዋል።

አያይዘውም በተያዘው የ2012 በጀት አመት ዘርፉን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሻገር የኮንትራት ውል አስተዳደር ስርዓት መዘርጋትን ጨምሮ የተለያዩ አሰራሮች ተግባራዊ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በርካታ ህገ – ወጥ እንቅስቀሴዎች መቀረፋቸውንና አዎንታዊ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆኑንም  ነው ሃላፊው ያስረዱት።

የምርት አቅርቦት ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ፣ በአገር ውስጥ የተቀመጠ የገበያ የመሸጫ ዋጋ ሁኔታ እና አንዳንድ የኮንትራት ችግሮች መኖር በግሉ ዘርፍ በተግዳሮትነት የቀረቡ ሲሆን÷ እነዚህንና ሌሎችንም ለመፍታት ከመቼውም ግዜ በላይ በቅርበት እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ምስጋኑ መጠቆማቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.