Fana: At a Speed of Life!

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በአሸባሪው ሕወሐት ተይዘው የነበሩትን የመሐል ሜዳ፣ ጨፋ ሮቢት፣ ሐርቡና መኮይ ከተሞችና አካባቢውን ነጻ አውጥቷል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በአሸባሪው ሕወሐት ተይዘው የነበሩትን የመሐል ሜዳ፣ ጨፋ ሮቢት፣ ሐርቡና መኮይ ከተሞችና አካባቢውን ነጻ አውጥቷል።
ጥምር የጸጥታ ኃይሎቹ በጥልቀት ገብተው በየቦታው የተበተነውን የአሸባሪውን ጀሌ በመልቀም ላይ በመሆናቸው፣ በጥምር የጸጥታ ኃይሎቹ የተመታው አሸባሪ ኃይል ዘርፎና አውድሞ፣ መሣሪያውንም ይዞ እንዳይወጣ የየአካባቢው ሕዝብ ተደራጅቶ መንገድ በመዝጋት፣ የአሸባሪውን ጀሌዎች በመማረክ፣ እምቢ ባሉትም ላይ ርምጃ በመውሰድ የተለመደ ጀግንነቱን እንዲደግም በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ቀርቦለታል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.