Fana: At a Speed of Life!

በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና  ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍፃሜ ውድድር የተሳተፈው አትሌት ልኬነህ አዘዘ በ7:44.06 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አምጥቷል።

ሌላው በውድድር የተካፈለው ኢትዮጵያዊ አትሌት ድርባ ግርማ በ7:50.63 በሆነ ሰዓት 4ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ዲፕሎማ አግኝቷል።

በተመሳሳይ በ800 ሜትር የወንዶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር በምድብ አንድ የተካፈለው  ኤርሚያስ ግርማ በ1:47.96 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ውድድር አልፏል።

በዚሁ ርቀት የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ከምድብ ሦስት መርሲሞይ ካሳሁን በ1:46.95 በሆነ ሰዓት 3ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ውድድር አልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.