Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ በፍጥነት ለማገገም ሀገራት በትብብር ሊሰሩ ይገባል-ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ በፍጥነት ለማገገም ሀገራት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ አሳሰቡ፡፡
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በዘንድሮው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ላይ በበይነ መረብ ባደረጉት ንግግር ፥ዓለም ዛሬ በአንድ ክፍለ ዘመን ውስጥ የማይታዩ ትልልቅ ለውጦች እያሳየች እንደምትገኝ አብራርተዋል፡፡
 
ከዚህም ውስጥ በዋነኝነት የኮሮና ቫይረስ መሆኑን በመጥቀስ ይህንን ወረርሽኝ እንዴት እናሸንፍ እና በቫይረሱ ምክንያት የተፈጠረውን የኢኮኖሚ ቀውስ እንዴት እንመክት የሚሉት አለም አቀፍ ትኩረት እና ምላሽ እንደሚሹ ጠቁመዋል፡፡
 
ለጥያቄዎቹ ምላሽ ለማበጀትም የዘመናችንን የእድገት ፍጥነት መሰረት በማድረግ ረጅም የታሪክ ዑደቶችን በማመሳከር እና የነገሮችን የለውጥ ሂደት በመመልከት የአለም ሀገራት ለቀውሱ መፍትሄ መፈለግ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት፡፡
 
አለማችን በችግር ጊዜ አዳዲስ እድሎችን መፍጠር አለባት ያሉት ፕሬዜዳንት ሺ ጂንፒንግ ፥ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በቀላሉ ለማለፍ በትብብር እና በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
 
በኮቪድ-19 ምክንያት የተፈጠረውን ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ቀውስ በፍጥነት እንዲያገግም ለመስቻል ሀገራት የትብብር መንፈስ በማዳበር በጋራ መስራት እንደሚገባቸውም ነው የጠቆሙት።
 
የቀዝቃዛ ጦርነት አስተሳሰብን በማስወገድ ሰላማዊ አብሮ የመኖር እና በትብብር ችግሮችን የመፍታት አስተሳሰብ ልንገነባ ይገባል ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ያመለክታል፡፡
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.