Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ አመጣጥ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂደው ልዑክ ቻይና ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ቫይረስ አመጣጥ ዙሪያ ጥናት የሚያካሂደው የዓለም ጤና ድርጅት ልዑክ ቻይና ቤጂንግ ገብቷል።

በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ቀውስ እያስከተለ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አመጣጥ ሁኔታ በርካታ ሀገራትን እና ድርጅቶችን ሲያወዛግብ ቆይቷል።

በተለይም አሜሪካ እና አጋሮቿ ቫይረሱ በቻይና ላቦራቶሪ የተፈበረከ መሆኑን በመግለፅ ለዚህም ተጨባጭ መረጃ እንዳላቸው በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም ቻይና ቫይረሱን መፈብረኳ ሳያንስ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመደበቅ ቫይረሱ በቀላሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲዛመት አድርጋለች ሲሉም ይወቅሳሉ።

ቤጂንግ በበኩሏ በሀገራቱ ዘንድ በተለያየ ጊዜ ሲቀርብባት የነበረውን ወቀሳ መሰረተ ቢስ ውንጅላ በማለት ስታጣጥል ቆይታለች።

በሀገራቱ መካካል ለወራት የዘለቀውን እሰጣ ገባ እልባት ለመስጠም የዓለም ጤና ድርጅት የላከው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በትናንትናው ዕለት ቤጂንግ ደርሷል።

ባለሙያዎቹ በቻይና ቆይታቸው በኮሮና ቫይረስ አመጣጥ እንዲሁም ቤጂንግ መጀመሪያ ላይ ቫይረሱን ለመቆጣጠር ባከናወነቻቸው ስራዎች ዙሪያ ጥናት እንደሚያካሂድ ነው የተነገረው።

ምንጭ፣ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.