Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ስድስት ተጨማሪ ሰዎች ተገኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 35 እንዳደረሰው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ አንደኛው ደግሞ ከድሬዳዋ ሲሆን፥ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው የ35 ዓመት እና የ30 አመት ወንዶች ሲሆኑ፥ መጋቢት 10 መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጡ ናቸው ተብሏል።

ሁለቱም ዜጎች አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የገቡ መሆናቸውንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው።

ሶስተኛው የ28 ዓመት ወጣት፣ አራተኛው የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

ሰዎቹ ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ መሆኑም ተገልጿል።

ስድስተኛዋ ሰው የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት መሆኑም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.