Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ዙሪያ የሚስተዋለው መዘናጋት የሃገሪቱን የጤና ሥርዓት ጫና ውስጥ ሊከተው ይችላል- የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለው መዘናጋት የኮቪድ19 ስርጭት እንዲባባስ ከማድረግ ባሻገር የሃገሪቱን የጤና ሥርዓት ጫና ውስጥ ሊከተው እንደሚችል የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስትር ዲኤታዋ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት እየተሻሻለና ለውጥ እያሳየ ቢሆንም በርካታ ቀሪ ተግባራት አሉት ብለዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት መጠን እየጨመረ ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው መዘናጋት ደግሞ ሃገሪቱ ካላት የጤና ሥርዓት ጋር ሲነጻጸር ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ሃገሪቷ ያላት የመመርመር አቅም ቢጨምርም በቫይረሱ እየተያዘ ያለው ሰው ደግሞ በዚያው ልክ መጨመሩ ሥርዓቱን ጫና ውስጥ ከቶታል ነው ያሉት።

ሚሊኒየም፣ ኤካ ኮተቤና ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታሎች በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ያለባቸውን ታካሚዎች በማስተናገዳቸው እየተጨናነቁ መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዋ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለህክምና የሚያግዙ መድኃኒትና ግብአቶች ከታካሚዎች ቁጥር ጋር እንደማይመጣጠን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.