Fana: At a Speed of Life!

በኮቪድ-19 ሳቢያ ከ156 ሚሊየን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል-ተመድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በኮቪድ-19 ምክንያት አሁን ለይ ከ156 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ ) ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ የኮሮና ቫይረሰ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ህጻናትላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን አንስቷል፡፡

ሀገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከሚወስዷቸው እርምጃዎች ጋር ተያይዞም ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ለመሆን መገደዳቸው ተመላክቷል፡፡

አሁን ላይም  19 በሚሆኑ ሀገራት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ እንዲዘጉ ተደርገዋል ፡፡

ይህን ተከትሎም ከ156 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

ስለሆነም ሀገራት አስፈላጊውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ትምህርት ቤቶችን ስራ ማስጀመር እንዳለባቸው ድርጅቱ አሳስቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.