Fana: At a Speed of Life!

በኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ የ60 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ100 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ በትንሹ የ60 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
ጀልባዋ ከዋና ከተማዋ ኪንሻሳ በስተ ምሥራቅ በምሽቱ እየተጓዘች ከዓለት ጋር መጋጨቷን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡
ጀልባዋ ከመጠን በላይ ሰዎችን የጫነች መሆኑ የተነገረ ሲሆን በኮንጎ ወንዝ ነው የመስጠም አደጋ እንዳጋጠማት ተነግሯል፡፡
በዚህም በትንሹ 60 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል 300 ሰዎችን ከአደጋው ማትረፍ መቻሉም ተገልጿል፡፡
የኮንጎ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ስቲቭ ምቢካይ ለጀልባው መስጠም ተጠያቂ የሆኑ እንዲከሰሱ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
ጀልባዋ ከ700 በላይ ተሳፋሪዎችን ጭና እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.