Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ኢ ቲ አር ኤስ 1 ኬ ኤም የተባለ ሮኬት ሰራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ኢ ቲ አር ኤስ1 ኬ ኤም የተባለ ሮኬት በዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ትብብር መሰራቱ ተገልጿል።
ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የገንዘብ ድጋፍና ትብብር( ETR S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት መስራቱን በዛሬው እለት አስታውቋል።
ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ ከዚህ በፊት ከአከባቢው ያገኘውን የተለያዩ ቁሳቁስ በመጠቀም ኤክስካባተር መኪና እንዲሁም የቆሻሻ ማፈሻ መኪና ሰርቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በቅርቡም የተሳካ የማስወንጨፍ ሙከራ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
ወጣቱ የሰራው ሮኬት አንድ ኪሎ ሜትር ድረስ የመወንጨፍ አቅም ያለው መሆኑንና፥ ሮኬቱን የሚሸከመው መኪናም አብሮ መሰራቱ ታውቋል።
ለወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ የተደረገው ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.