Fana: At a Speed of Life!

በወምበራ ወረዳ 1 ሺህ 395 ዜጎች ወደ ማዕከል ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ እየተካሄደ ያለውን ሕግ የማስከበር ሥራ ተከትሎ 1 ሺህ 395 ዜጎች ወደ ኮንግ ማዕከል ተመልሰዋል፡፡
ከ1 ሺህ 395 ዜጎች መካከል 99 ያህሉ ሕጻናት መሆናቸው ተገልጿል።
በቀጣናው የተገኘውን ሰላም ተከትሎ እየተካሄደ በሚገኘው የሕዝብ ውይይት በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ከጫካ ወደ ማዕከል እየተመለሱ መሆኑን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
በወረዳው በጸረ ሰላም ኃይሎች ምክንያት ወደ ጫካ ገብተው የነበሩ ዜጎች በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ አካላት በተደረገ ሕግ የማስከበር ሥራ ህብረተሰቡ ወደ ነባር ቀየ እተመለሱ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ወደ ማዕከል ለተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የሰብዓዊ እርዳታው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡
ሰላም ለማስፈንና የህብረተሰቡን ደኅንነት ለማስጠበቅ ሲባል እየተካሄደ ያለው ሕግ የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.