Fana: At a Speed of Life!

በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምሁራን የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምሁራን የውይይት መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተካሂዷል።
በውይይትት መድረኩ ላይ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ምሁራን በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ተደርግላቸዋል።
ገለጻው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተደረገ ሲሆን፥ ምሁራኑ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት እና ድርጅቶች የተውጣጡ ናቸው።
ውይይቱን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ናቸው።
አቶ ዛዲግ አብርሃ በዚሁ ወቅት፥ ህወሓት ከለውጡ ጀምሮ የሄደበትን መንገድ እና የፈፀመውን የሃገር ክህደት ወንጀል በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም በውይይቱ ዘመቻ የህግ የበላይነት ለሀገር ህልውና፣ በድህረ ህውሓት ኢትዮጵያ – የምሁራን ሚና ምን መሆን እንዳለበት፣ የጁንታው ክህደት፣ ያደረገው አረመኔያዊ ተግባር፣ የሠራዊታችን የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳሰዋል።
አስተያየት የሰጡ ምሁራን፣ ፅንፈኛው ሀይል በሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን ድርጊት ያወገዙ ሲሆን፥ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅም ጠይቀዋል።
መሰል ችግሮች ማንነትን መሰረት አድርገው እንዳይከሰቱ ስራዎች መከናወን እንዳለባቸው አመልክተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.