Fana: At a Speed of Life!

በወዳጅነት ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛምቢያ አቻው ተረታ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በወዳጅነት ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛምቢያ አቻው ለሁለተኛ ጊዜ ተሸነፈ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን (ቺፖሎፖሎዎቹ) በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሁለተኛ ጊዜ የወዳጅነት ጨዋታ አድርገዋል።

በጨዋታውም በዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን (ቺፖሎፖሎዎቹ)በቺፖሎፖሎዎቹ የ3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ከሶስት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን (ቺፖሎፖሎዎቹ) ያደረጉት የመጀመሪያው የወዳጅነት ጨዋታ በዛምቢያ 3ለ 2አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.