Fana: At a Speed of Life!

በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የግዳጅ ቀጠና የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት የዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ከዞኑ የህዝብ ተወካዮችና ሃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ የዕዙ ዋና አዛዥ እንደተናገሩት÷ማህበረሰቡ ጠላት በተስፋ መቁረጥ ላይ ሆኖ የሚለቃቸውን የውሸት ፕሮፖጋንዳዎች ወደ ጎን በመተው ለሠራዊቱ የድል አድራጊነትና እንደከዚህ ቀደሙ አብሮነቱ እና ደጀንነቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደሪ ስቡህ ገበያው በበኩላቸው÷ የዋግ ህዝብ ለጠላቱ የማይበገር እና በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ታሪኩን አስጠብቆ የሚቀጥል መሆኑን አንስተዋል፡፡
አሁንም የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሠለፍ የጠላትን ቅስም ለመስበር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
የዋግኽምራ ብሔረሰብ ህዝብ ተወካዮች በቀጠናው የሚገኘው ሰራዊት ለአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት ሠርቶ በማስረከብ በጎ ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል ብለዋል።
የሀገሪቱን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የአካባቢን የፀጥታ ሃይል ማጠናከርና ለሠራዊቱ ደጀን በመሆን ኢትዮጵያን በድል ለቀጣይ ትውልድ እናሻግራለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዋግኽምራ ብሔረሰብ የህዝብ ተወካዮች አንድነትና ፍቅራቸውን ለሠራዊቱ ለመግለፅ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትን ለዕዙ አመራሮች በስጦታ አበርክተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.