Fana: At a Speed of Life!

በውቅሮ ከተማ ጊዜያዊ የአስተዳደር መዋቅር የመዘርጋት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በውቅሮ ከተማን ጊዜያዊ የአስተዳደር መዋቅር የመዘርጋት ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ በመሩት የውይይት መድረክ  የውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱም የኤሌክትሪክ፣ የውሃና ሌሎች የመሰረተ ልማት ችግሮች በአጭር ጊዜ እንዲፈታ ጠይቀዋል።

ነዋሪዎቹ አሁንም ከቴሌኮሙኒኬሽን፣ ከባንክ፣ ከህክምና እንዲሁም ከትራንስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ችግሮች እንዳሉባቸው ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊቱ ውቅሮ ከተማ ከገባ ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ ሰላምና መረጋጋት መፈጠሩን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በአፋጣኝ መዋቅሩን በመዘርጋት የህዝቡን ደህንነት ማስጠበቅና የመልሶ ግንባታ ሥራ ሊጀምር ይገባል ብለዋል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለሰቦች ለመንግስት ማስረከብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ህብረተሰቡ ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ ያነሳቸው ጥያቄዎች በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን አመራሮች በራሱ ፈቃድ ነጻ ሆኖ እንዲመርጥ ለማድርግ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ የትግራይ ህዝብ ሰላምና ልማቱን ለማረጋገጥ በጋራ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸው፤ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ህዝቡ የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.