Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺህ በልጧል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺህ በለጠ፡፡

መነሻውን ቻይና ሁቤ ግዛት ያደረገው ኮሮና ቫይረስ አሁን ላይ የአለም ስጋት መሆኑን ቀጥሏል፡፡

በዚህም ከ170 በላይ ሃገራትን አዳርሷል፡፡

ይህ ዘገባ እስከሚጠናቀርበት ሰዓት ድረስ በዓለም የሟቾች ቁጥር 30 ሺህ 857 የደረሰ ሲሆን፥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 665 ሺህ 616 ደርሷል፡፡

በፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው ቫይረሱ ጣሊያን፣ ስፔን፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ኢራን፣ ጀርመን እና ፈረንሳይን ክፉኛ እየጎዳ ይገኛል፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንሰ ዩኒቨርሲቲ መረጃም በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 124 ሺህ 686 ሲሆን ይህም ከዓለም ቀዳሚ አድርጓታል፡፡

በጣሊያን 96 ሺህ 472፣ በቻይና 82 ሺህ፣ በስፔን 73 ሺህ 57፣ በጀርመን 57 ሺህ 697 እንዲሁም በፈረንሳይ 38 ሺህ 105 ሰዎቸው በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

ጣሊያን በሟቾች ቁጥር ቀዳሚ ስትሆን 10 ሺህ 23 ዜጎቿን ተነጥቃነች፡፡

በስፔን 5 ሺህ 982፣ በቻይና 3 ሺህ 182፣ በኢራን 2 ሺህ 517 እንዲሁም በፈረንሳይ 2 ሺህ 314 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

141 ሺህ 746 ሰዎችም ከቫይረሱ አገግመው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡

ሃገራትም የቫይረሱን ስርጭት ለማስቆም ድንበር ከመዝጋት ጀምሮ ማንኛውንም የህዝብ እንቅስቃሴ በማገድ ላይ ይገኛሉ፡፡

 

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን እና ጆን ሆፕኪንሰ ዩኒቨርሲቲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.