Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1ሚሊየንን አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን አልፏል፡፡

እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ 1 ሚሊየን 2 ሺህ 561 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ተብሏል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከ33 ሚሊየን 311 ሺህ በላይ ሆኗል፡

በአንጻሩ ከ24 ሚሊየን 639 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ኮሎምቢያ ቫይረሱ በክፈተኛ ደረጃ የጸናባቸው ሃገራት ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.