Fana: At a Speed of Life!

በዓለም በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ64 ሺህ በለጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ64 ሺህ መብለጡ ተገለፀ፡፡

በፈረንጆቹ 2019 መገባደጃ ላይ በቻይና ውሃን ግዛት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የአለም ስጋት መሆኑን ቀጥሏል፡፡

ይህ ዘገባ እስከሚጠናቀርበት ሰዓት ድረስም በዓለም 1 ሚሊየን 204 ሺህ 246 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 64 ሺህ 806 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አጥተዋል፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃም በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 312 ሺህ 245 ደርሷል፡፡

በስፔን 126 ሺህ 168 ፣ በጣሊያን 124 ሺህ 632፣ በጀርመን 96 ሺህ 92 እንዲሁም በፈረንሳይ 90 ሺህ 853 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

የሟቾች ቁጥርም ቀን በቀን እያሻቀበ የመጣ ሲሆን፥ በዚህም ጣሊያን ቀዳሚ ስትሆን 15 ሺህ 362 ዜጎቿ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በስፔን 11 ሺህ 947 ሰዎች ለህልፈት ሲደረጉ በፈረንሳይ 7 ሺህ 560 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በዓለም 247ሺህ 340 ሰዎችም ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.