Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኮሮናቫይረስ ክትባት ስራ የተሰበሰበው ገንዘብ ከ10 ቢሊየን ዶላር አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ዙሪያ ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እየተሰበሰበ ያለው ገንዘብ 10 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን የአውሮፓ ህብረት ገለፀ።

ባሳለፍነው ወር በአውሮፓ ህብረት አስተባባሪነት ዓለም አቀፍ የኮሮና ክትባት የማፈላለግ ስራ የገንዘብ ድጋፍ ዘመቻ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮን ዴር ላይ እንደተናገሩት እስካሁን በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻው 10 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተገምቷል።

ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ላይ በተጀመረው ዘመቻው ላይ የዓለም ሀገራት መሪዎች ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት ከ8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውም ይታወሳል።

በወቅቱም በአጠቃላይ ከተባበሩት መንግስታት በተጨማሪ ከ30 በላይ ሀገራት ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ከተዋጣው ገንዘብ ለክትባት ስራ፣ በህክምናው ዙሪያ ለሚደረግ ምርምር እና የቫይረሱ ተጠቂዎችን ለመለየት የምርመራ ስራን ለማጠናከር የሚልው መሆኑን የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል።

ምንጭ፦ aljazeera.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.