Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት አያል የወርቅ ሜዳልያ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት አያል ዳኛቸው የወርቅ ሜዳልያ አሸነፈች፡፡

በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር ለኢትዮጵያ ሁለተኛው የወርቅ ሜዳልያ በመሆን ተመዝግቧል፡፡

አትሌት አያል ዳኛቸው በ2:02.96 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያ ለሀገሯ አስመዝግባለች።

በሌላ በኩል በ1500 ሜትር ወንዶች ውድድር የተሳተፋት አትሌት ወገኔ ሰብስቤ በ3:37.86 በሆነ ሰዓት 2ኛ ፣አትሌት መልኬነህ አዘዘ በ3:40.22 በሆነ ሰዓት 3ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር እና የነሀስ ሜዳልያዎችን ማስገኘታቸውን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.