Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና  ለተካፈለው ልኡክ የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ-ናይሮቢ በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ በድል ለተመለሰው ልኡክ የማበረታቻ  ሽልማት ተበርክቶለታል።

ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በ18ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ በ3 ወርቅ፣ በ7 ብር እና በ2 ነሀስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች ከዓለም 4ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ላጠናቀቀው የአትሌቲክስ ቡድን ፌዴሬሽኑ  የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል።

በሻምፒዮናው የወርቅ ሜዳሊያ ላመጣ 25 ሺህ ብር፣ የብር ሜዳሊያ ላመጣ 18 ሺህ  ብር፣  የነሃስ ሜዳሊያላመጣ 10 ሺህ ብር ለዲፕሎማ 6 ሺህ ብር እና ለተሳትፎ 3 ሺህ  ብር ለአሰልጣኞችና ባለሙያዎች እንዳስመዘገቡት ውጤት መሸለማቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.