Fana: At a Speed of Life!

በዓሉን ስናከብር በመረዳዳት ሊሆን ይገባል-የከተራ በዓል ታዳሚዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ በአዲስ አበባ የከተራ በዓልን የታደሙ የእምነቱ ተከታዮች ተናገሩ።
የከተራ በዓል በዛሬው ዕለት በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሯል።
ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት አስያየታቸውን የሰጡ በዓሉን በጃን ሜዳ የታደሙ የእምነቱ ተከታዮችም÷ በዓሉን የተቸገሩ ወገኖቻችን እና የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
እንዲሁም የበዓሉን ዓላማ ባከበረ መልኩ ሊከበር ይገባል ነው ያሉት።
የመንግስት ጥሪ ተከትሎ ከመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በዓሉን ማክበራችን ደግሞ የዘንድሮውን በዓል የተለየ ያደርገዋል፤ ሃገራዊ አንድነትንም ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል ተሳታፊዎቹ።
ተሰባስቦ በዓል ማክበር በዳያስፖራውም ሆነ ሃገር ውስጥ በሚገኘው ኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚፈጥረው ደስታ እና በበዓሉ አከባበር ላይ የሚፈጥረው ድባብም ከፍ ያለ መሆኑንም ነው ያነሱት።
በዓሉ በአዲስ አበባ በጃን ሜዳ በአቅራቢያ የሚገኙ አድባራትና ገዳማት ታቦታት የጥምቀት በዓልን በጋራ የሚያከብሩ ሲሆን፥ ዛሬ ከአድባራትና ገዳማት ጉዞ በመጀመር ታቦታቱ ምሽት ላይ ጃን ሜዳ የሚያድሩ ይሆናል።
በነገው ዕለት ታቦታቱ ከከተራ (ከማደሪያው) ቦታው በመነሳት በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደየ ደብራቸው ይመለሳሉ።

በፌቨን ቢሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.