Fana: At a Speed of Life!

በዓረብኛ ቋንቋ ከሚጽፉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጃይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዓረብኛ ቋንቋ ከሚጽፉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ።

ውይይቱ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች እና በቀጣይ የሃገሪቱን በጎ ገጽታ ለውጭው ዓለም በተለይም በመካከለኛው ምስራቅና በዓረቡ ዓለም ለማስተዋወቅና አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በኢትዮጵያና በመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም በዓረቡ ዓለም መካከል በርካታ የሚያስተሳስሩ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና የህዝቦች ትስስር መኖሩን አንስተዋል።

ከዚህ አንጻርም የጋራ የሆኑ እሴቶችን መሰረት ያደረገ መንገድ በመከተል መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በቀጣይም የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ ለመገንባት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.