Fana: At a Speed of Life!

በዘንድሮው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ዘርፍ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2012 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ከ3 ቢሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር በላይ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ገቢው የእቅዱ 81 በመቶ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታው አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገልጸዋል፡፡

የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የ14 በመቶ እድገት ወይም የ3 መቶ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብልጫ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ የግብርናው ዘርፍ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በማስመዝገብ ቀዳሚ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 406 ሚሊየን ዶላር የተመዘገበበት ሲሆን፣ የማዕድን ዘርፉ ደግሞ 208 ሚሊየን ዶላር ማስመዝገቡን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንደ ኤሌክትሪክ ያሉ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርትና አገልግሎቶች ደግሞ ቀሪውን ድርሻ ይዘዋል፡፡

የኮንትራት አስተዳደር ስርዓት መዘመን፣ የኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር መጠናከር እና በተቋማትና ክልሎች መካከል ቅንጅታዊ አሰራር ውጤታማ መሆኑ ለወጪ ንግድ አፈጻጸሙ ስኬታማነት ዋነኛ ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.