Fana: At a Speed of Life!

በዚህ ዓመት 5 ሚሊየን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል – ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ መርሃ ግብር የመጀመሪያዎቹ 450 ሺህ ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ እንዲኖራቸው እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት ደግሞ 5 ሚሊየን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ይኖራቸዋል ብለዋል።

የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማድረግ አንዱ አካል መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.