Fana: At a Speed of Life!

በየመን በሚሳኤል ጥቃት በትንሹ የ80 ወታደሮች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በየመን ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈፀመ የሚሳኤል ጥቃት በትንሹ የ80 ወታደሮች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

በየመን ማዕከላዊ ግዛት ማሪብ ከተማ በሚገኘው የጦር ካምፕ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸውን ካጡ የሰራዊቱ አባላት በተጨማሪ በርካቶች መቁሰላቸው ተነግሯል።

የጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ነው የሀገሪቱ መንግስት ባለስልጣናት ያስታወቁት።

ከየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በ170 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የተፈፀመው ጥቃት ዋንኛ ኢላማው ለፀሎት በመስጊድ የተሰበሰቡ ሰዎች እንደነበሩ ወታደራዊ ምንጮች ተናግረዋል።

የየመን መንግስት ለጥቃቲ የሀውቲ አማፅያን ቡድንን ተጠያቂ ማድረጉም ነው የተገለፀው።

ሆኖም ግን ለሚሳኤል ጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል አልተገኘም ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.