Fana: At a Speed of Life!

በየመን በእስር ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ በርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አልፏል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን በደረሰው የእስር ቤት ቃጠሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው ማለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፥ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያውያን ትክክለኛ ቁጥር እየተጣራ ነው ብለዋል።

በኦማን መዲና ሙስካት የሚገኘው የኢትዬጵያ ኤምባሲም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ከአደጋው የተረፉትን ከአካባቢው ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ 733 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ነው አምባሳደሩ በመግለጫቸው ያነሱት።

የህዳሴው ግድብ ድርድር ጉዳይም  የአፍሪካ ህብረትን እየመራች በምትገኘው በዲሞክራቲክ ኮንጎ አማካይነት እንዲቀጥል ለማስቻል የሚረዱ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አምባሳደሩ  አስታውቀዋል።

በትግራይ ክልል እስካሁን በተሰራው የሰብአዊ ድጋፍም  የማድረስ ስራ 3ነጥብ 8 ሚሊየን ህዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሳምንቱ በተካሄዱ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ስራዎች በፀጥታው ምክርቤት አባል የሆኑ በኢትዮጵያ ያሉ አምባሳደሮችን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማወያየት እንደተቻለ በመግለጫው ተመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

በፋሲካው ታደሰ እና ይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.