Fana: At a Speed of Life!

በደሴ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ቆመው የነበሩ የልማት ስራዎች በቅርቡ እንደሚጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ወረራ ምክንያት ቆመው የነበሩ የልማት ስራዎች በቅርቡ እንደሚጀመሩ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገለጸ።
 
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የሽብር ቡድኑ ህወሓት ደሴ ከተማን በወረራ መያዙን ተከትሎ ቆመው የነበሩ የልማት ስራዎች እንዲቀጥሉ እየተሠራ ነው ብለዋል።
 
የቄራ አስፋልት መንገድ፣ የተጀመሩ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የመናኸሪያ እና የመፋሰሻና የኮብልስቶን መንገዶች ስራ በቅርቡ እንደሚጀር ጠቁመዋል።
 
በፌዴራል መንግስቱ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ከንቲባው፥ የዓለም ባንክና በራስ በጀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በቶሎ ለማስጀመርም ምክክር መደረጉን ገልጸዋል።
 
በሚቀጥለው ሳምንት ምክር ቤት ጋር ውሳኔ በማሳለፍ ስራዎቹ እንደሚጀመሩ ገልጸው፥ ፕሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ ለመጨረስ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
 
አሸባሪው ቡድን በከፈተው ወረራ ልማቶቹ ቢቋረጡም በመልሶ ግንባታው ምዕራፍ ትኩረት ተሰጥቷቸው ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል፡፡
 
በከድር መሀመድ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.